እንኳን ወደ ማራኪ ጠላ እና ጠጅ በደህና መጡ፣ ባህላዊነት ከጣዕም ጋር የሚገናኝበት ቦታ ነዉ።እኛ የኢትዮጵያን ባህላዊ መጠጦችን እውነተኛ በሆነ መልኩ እንዘጋጃለን፤
ይህም ባህላችንን የሚያስተዋዉቅ እና ልዩ የሆነ የመጠጥ ተሞክሮ የሚሰጥ ነው። በዋናነት ሁለት አይነት የኢትዮጲያ ባህላዊ መጠጦችን እናዘጋጃለን እነሱም:ጠላ፣ ከገብስ፣
ከጌሾ እና ከብቅል የሚዘጋጅ ባህላዉ መጠጥ ነው። ሌላኛዉ ደግሞ ጠጅ ሲሆን፣ሲሆን ከንፁህ ማርና ጌሾ የተዘጋጀ አስደናቂ መጠጥ ነው::
ኢትዮጵያ በባህላዊነቷ የታወቀች ሀገር ናት፣ መጠጦቿም የዚህን ባህላዊነት በሙሉ ያንጸባርቃሉ። እኛ የምንጠቀመው እያንዳንዱ የመጠጥ አዘገጃጀት በትውልድ ላይ ተላልፎ የመጣ ሲሆን፣ የኢትዮጵያውያንን ባህላዊ የመጠጥ ማቀናበሪያ ቴክኒኮች በትክክል የሚያሳይ ነው። የእኛ የማቀናበሪያ ዘዴዎች ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን እና ከአካባቢ የሚገኙ ንጥረ ነገሮችን በመጠቀም ላይ ያተኮረ ነው፣ ይህም በአካባቢ ገበሬዎች ድጋፍ እንዲደርስና የተስተናጋጅነትን ተስፋ እንዲያሳይ የሚያደርግ ነው።
ማራኪ ጠላ እና ጠጅ እንደ አዉሮፓ አቆጣጠር በ2019 ዓ.ም የኢትዮጵያን ባህል እና ታሪክ በሚወዱ ጀግና ኢትዮጲያውያን ተመሰረተ። ማራኪ ጠላ እና ጠጅ ከመጠጥ ማምረቻ እና መሸጫ በተጨማሪ የኢትዮጵን ባህል፣ ቅርስ እና ማሀበረሰብ የሚያስተዋዉቅ ተቋም ነዉ። የድርጅታችን መስራቾች ጥንታዊ እና ታሪካዊ የሆነዉን የኢትዮጵያ ባህላዊ መጠጦች አዘገጃጀት ዘዴ በማጥናት ለዘመናዊዉ አለም አቅርበዋል።
ጥልቅ በሆነ የመጥመቅ ችሎታ እና ለአካባቢ ዘላቂነት ባለን ቁርጠኝነት ደረጃዉነ የጠበቀ የባህላዌ መጠጦች ማምረቻ ተቋም ። ከሁሉም ለየት የሚያደሪገን ደግሞ እያንዳንዱ ግብአቶቻችንን ከራሳችን እርሻ በራሳችን ገበሬዎች ማምረት መቻላችን ነዉ።
ከእርሻ ቦታችን ጀምሮ እስከ ተዘጋጅቶ ያለቀ መጠጣችን ድረስ እያንዳንድ እርምጃዎቻችን በቁጥጥር እና በጥራት ነው የሚከናወኑት።
የኢትዮጵያን ባህል በትክክለኛ መልኩ የሚያንፀባርቀውን ጠላችንን እና ጠጃችንን ጥንታዊዉን የአጠማመቅ ዘዴ ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ ጋር በማቆራኘት አናዘጋጃለን።