ማራኪ ጠላ እና ጠጅ እንደ አዉሮፓ አቆጣጠር በ2019 ዓ.ም የኢትዮጵያን ባህል እና ታሪክ በሚወዱ ጀግና ኢትዮጲያውያን ተመሰረተ። ማራኪ ጠላ እና ጠጅ ከመጠጥ ማምረቻ እና መሸጫ በተጨማሪ የኢትዮጵን ባህል፣ ቅርስ እና ማሀበረሰብ የሚያስተዋዉቅ ተቋም ነዉ። የድርጅታችን መስራቾች ጥንታዊ እና ታሪካዊ የሆነዉን የኢትዮጵያ ባህላዊ መጠጦች አዘገጃጀት ዘዴ በማጥናት ለዘመናዊዉ አለም አቅርበዋል።
ጥልቅ በሆነ የመጥመቅ ችሎታ እና ለአካባቢ ዘላቂነት ባለን ቁርጠኝነት ደረጃዉነ የጠበቀ የባህላዌ መጠጦች ማምረቻ ተቋም ። ከሁሉም ለየት የሚያደሪገን ደግሞ እያንዳንዱ ግብአቶቻችንን ከራሳችን እርሻ በራሳችን ገበሬዎች ማምረት መቻላችን ነዉ። ከእርሻ ቦታችን ጀምሮ እስከ ተዘጋጅቶ ያለቀ መጠጣችን ድረስ እያንዳንድ እርምጃዎቻችን በቁጥጥር እና በጥራት ነው የሚከናወኑት
የኢትዮጵያን ባህል በትክክለኛ መልኩ የሚያንፀባርቀውን ጠላችንን እና ጠጃችንን ጥንታዊዉን የአጠማመቅ ዘዴ ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ ጋር በማቆራኘት አናዘጋጃለን :: ከእርሻ ቦታችን ጀምሮ እስከ ተዘጋጅቶ ያለቀ መጠጣችን ድረስ እያንዳንድ እርምጃዎቻችን በቁጥጥር እና በጥራት ነው የሚከናወኑት።
የኢትዮጵያ ቅርስ የሆነዉን ጠላ እና ጠጃችንን ለአለም
በማስተዋወቅ አለም አቀፍ አምባሳደር ለመሆን።